የትግራይና የኤርትራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ከስምምነት ላይ ተደረሰ

58

መጋቢት 17/ 2013 (ኢዜአ) የትግራይ እና የኤርትራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር በቀጣይ ሊሰሩ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት መደረሱን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሀም በላይ ገለፁ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የልዑካን ቡድን ውስጥ የተካተቱት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሀም በአስመራ የነበረውን ጉብኝት በተመለከተ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ወንድማዊ ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ በመሰረተ ልማት ስራዎች ለማስተሳሰርም ከስምምነት ላይ መደረሱን ኢቢሲ ዘግቧል።

በዚህም በቀጣይ በጋራ ሊሰሩ የሚችሉ ፕሮጀክቶች ተቀርፀው ወደ ስራ ለመግባትም ከመግባባት ላይ ተደርሷል።

ኤርትራ ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት ስምምነት ላይ መደረሱን መገለጹ ይታወሳል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው ልዑካን ቡድን በአስመራ የነበረውን የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አናጠቅቆ አዲስ አበባ ገብቷል።


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም