በተለያዩ ሚሲዮኖች ለተመደቡ የዳያስፖራ ክላስተር አስተባባሪዎችና ዲፕሎማቶች የስራ መመሪያ ተሰጠ

71

መጋቢት 6 / 2013 (ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቅርቡ በተለያዩ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮኖች ለተመደቡ የዳያስፖራ ክላስተር አስተባባሪዎችና ዲፕሎማቶች የስራ መመሪያ መስጠታቸው ተገለፀ ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የሀብት አስተዳደር ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በተለያዩ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮኖች ለተመደቡ የዳያስፖራ ክላስተር አስተባባሪዎችና ዲፕሎማቶች የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

ሚኒስትሩ ስምሪቱን ለልዩ ተልዕኮ ዲፕሎማቶችን መመደብ በማስፈለጉ የተካሄደና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሚኒሲቴር መህፈት ቤቱን የሰው ኃይል አቅምን ከግንዛቤ ወስጥ በማስገባት ለዳያስፖራ ስራዎች ዲፕሎማቶቹ መመደባቸውን አብራርተዋል።

በተያያዘም በአሁኑ ወቅት የአገሪቱን ገጽታ የሚያጎድፉ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉ አካላት እንዳሉ አንስተው፤ ተመዳቢዎቹም ሆነ ሌሎች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ዲፕሎማቶች በየአገራቱ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር በመተባበር የአገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታን ለማስገንዘብ እንዲቻል ለዲጅታል ዲፕሎማሲ ስራዎች ትኩረት በመስጠት ስራቸውን ማከናውን አንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በበኩላቸው ዲፕሎማቶቹ የዳያስፖራውን የሀዝን እና ደስታ ጊዚያት በቅርበት እንዲካፈሉ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለተመዳቢ ዲሎማቶች መልካም የስራ ዘመን መመኘታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም