ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ የይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀዋል

59

መጋቢት 4/2013 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ከፌዴራልና ከክልል አመራሮች ጋር በመሆን የይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፈቱ፡፡

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እየተገነባ ያለው የፓርኩ የመጀመሪያ ምዕራፍ በከፊል ምርት ጀምሯል፡፡

እስካሁን ከተገነቡት 11 የምርት ቦታዎች ውስጥ 4 ቱ በማምረት ላይ ናቸው፡፡8 ተጨማሪ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች የገበያ ትስስር እና ሌሎች ፍላጎቶችን በመፍጠር የማሽን ተከላ ከተጠናቀቀ በኋላም ምርት ለመጀመር በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት በአቮካዶ ዘይት ፣በማር እና በቡና ኪኒን ማቀነባበር ላይ መሰማራታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም