በ387 ሚሊየን ብር የተገነባ የበለስ ጃዊ የሀይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክት ተመረቀ

69

ግልገል በለስ የካቲት 29/ 2013 (ኢዜአ)- በአማራ ክልል በ387 ሚሊየን ብር የተገነባ የበለስ ጃዊ የሀይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክት ተመረቀ ።

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገርና የውሀ ፣ የመስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ፕሮጀክቱን መርቀዋል ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኢዜአ እንደገለጹት ለፕሮጀክቱ ግንባታ የዋለው ገንዘብ በኢትዮጵያ መንግስት የተመደበ ነው።

ፕሮጀክቱ 132 ኪሎ ቮልት ሀይል በመቀበል 33 ኪሎ ቮልቱን ማከፋፈል የሚችል መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ ካሉት ዘጠኝ የሀይል መውጫ መስመሮች ውስጥ ሶስቱ ለስኳር ፋብሪካው ጥቅም ላይ የሚውሉ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ቀሪዎቹ መስመሮች በአካባቢው ለሚከናወኑ ኢንቨስትመንት ስራዎችና ለከተሞች አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም