የጉባኤው 10ኛ አመት የምስረታ በአል በጅማ እየተከበረ ነው

64

ጅማ የካቲት 27 /2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ 10ኛ አመት የምስረታ በአል በጅማ ከተማ እየተከበረ ነው ።

“ለሰላም አንሰራለን፤ ለሰለም እንኖራለን፤ዘረኝነትን እንፀየፋለን “ በሚል መሪ ቃል ዛሬ  ከቀትረ በኋላ ጀምሮ በአሉ እየተከበረ ይገኛል።

የጉባኤው ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሐን ታጋይ ታደለ በወቅቱ እንዳሉት ጉባኤው ከተመሰረተ ጀምሮ ለ10 አመት ሐይማኖት በኩልነትና በመከባበር እንዲጓዝ በማድረግ ሰለምን ለማስፈን ሲሰራ ቆይቷል።

ጠቅላይ ፀሐፊው አክለውም ጉባኤው የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን የሐይማኖት ግጭት ለማስመሰል የሚሰሩ አካላትን ለመከላከል ሲሰራ መቆየቱን አመልክተዋል።

የኢፌደሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬአለም ሽባባው በበኩላቸው “መንግሥት የሐይማኖት ተቋማት ለሐገራችን ሰላም ትልቅ ሚና እንዳላቸው ይገነዘባል” ብለዋል።

የሐይማኖት ተቋማት  መእመናን ሐይማኖታቸውን በነፃነትና በእኩልነት እንዲያራምዱ የማድረግ የማይተካ ሚና ያላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።

የጉባኤው የቦርድ አባል ቄስ ዶክተር ዋቅስዩም ኤዶሳ “የሐይማኖት ተቋማት ዋንኛ መልዕክታቸው ሰላምን ማወጅ ነው “ ሲሉ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም