በከተማዋ በህገ-ወጥ መንገድ ከተያዘ መሬት ውስጥ ከ1 ሺህ ሄክታር በላይ ወደ መሬት ባንክ ገቢ ሆኗል

54

አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2013(ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገው የመሬት ወረራ በህገ-ወጥ መንገድ መያዛቸው ከተረጋገጡ ከአንድ ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ መደረጉ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የስምንተኛ አመት የስራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

ጉባኤው የተለያዩ አጀንዳዎችን የያዘ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ የ2013 ዓ.ም ግማሽ አመት አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሞ ማጽደቅ አንደኛው ነው።

በጉባኤው ላይ የከተማዋን የመጀመሪያ መንፈቅ አመት እቅድ አፈጻጸም ያቀረቡት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ እንዳሉት፤ ከተማዋ የተስተዋለውን ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ ለመከላከል ግብረ ሃይል ተቋቁሞ መረጃ የማጥራት ስራ ተሰርቷል።

ለዚህም በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተደረገው የመሬት ወረራ በ632 ቦታዎች 1 ሺህ 338 ሄክታር መሬት በህገ ወጥ መንገድ መያዙ ተረጋግጧል ብለዋል።

በህገ ወጥ መንገድ የተወረሩት መሬቶችም በህጉ መሰረት እንዲመለሱ በማድረግ እስካሁን ከ 1 ሺ ሄክታር መሬት በላይ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ መደረጉን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም