በጋና እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው መልካም ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት--ም/ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ

50

የካቲት 25/2021 (ኢዜአ) በጋና እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው መልካም ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በዛሬው እለት ተሰናባቹን የአፍሪካ ህብረት ምክትል ኮሚሽነር አምባሳደር ክዌስ ኳሪተይ በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

አቶ ደመቀ ምክትል ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ የጋና አምባሳደር በነበሩበት ወቅት እንዲሁም በህብረቱ ምክትል ኮሚሽነርነታቸው ላበረከቱት አገልግሎታቸው አመስግነው ፤ በጋናና በኢትዮጵያ መካከል ያለው መልካም ግንኙነት መጠናከር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አያይዘውም በትግራይ ክልል እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ ድጋፍ አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የአፍሪካ ህብረት ጉዳዩን በመረዳት ለወሰደው አቋም፤ አድናቆታቸውን ለኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ኮሚሽነሩም በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ስለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው፤ ከኢትዮጵያን ጋር ያላቸውን ወዳጅነት እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም