ወጣቱ የድል በዓሉን የአድዋን ጀግኖች ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ አክብሮታል

57

የካቲት 23/2013 (ኢዜአ) ወጣቱ ትውልድ የአባቶቹን ታሪክ በማስታወስ ብቻ ሳይሆን ከታሪኩ ተምሮ ሃላፊነቱን ለመወጣት መዘጋጀት እንዳለበት ተገለጸ።

ወጣቶችና ፈረሰኞች የድል በዓሉን የአድዋን ጀግኖች ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ አክብረውታል ሲል የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገልጿል።

125ኛው የአድዋ ድል በዓል በክልሉ ከየካቲት 15 ጀምሮ በወረዳና በዞን ደረጃ በፓናልና በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከብር መቆየቱን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ከበደ ደሲሳ ለኢዜአ ገልፀዋል።

የቢሮ ሃላፊው እንደገለጹት በአድዋ ድል በዓል አከባበር ፈረሰኞች የነበራቸውን ተጋድሎና አስተዋፅኦ በሚያሳይ መልኩ መከበሩን ተናግረዋል።

ክብረ በዓሉ ለቀጣይ የአድዋ በዓላት በሚያዘጋጅና ትውልዱን በሚያበረታታ መልኩ መከበሩን ገልጸው በዓሉን ላደመቁት ፈረሰኞች ምስጋና አቅርበዋል።

የበዓሉ አከባበር የያኔውን ትውልድ በሚያስታውስ መልኩና የኢትዮጵያውያንን ሉዓላዊነት በሚያረጋግጥ መልኩ መከበሩ የአሁኑ ትውልድ ለቀጣይ ድል እንደሚያዘጋጅ ገልፀዋል።

ትውልዱ የአባቶቹን ታሪክ ለማስታወሰ ብቻ ሳይሆን ከእነሱ ተምሮ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ለመወጣትና ታሪክ ለመስራት ሊዘጋጅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።ቢሮው ለለ125ኛው የአድዋ ድል በዓል አከባበር ድምቀት ለነበሩት ፈረሰኞች ምስጋና አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም