125ኛው የዓድዋ የድል በዓል እየተከበረ ነው

70

የካቲት 23/ 2013 (ኢዜአ) 125ኛው የዓድዋ የድል በዓል በአዲስ አበባ በዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

በክብረ በዓሉ ላይ ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የጀግኖች አርበኞች ማህበር አባላትን እና በርካታ እንግዶች ታድመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም