በብዙ መስዋዕትነት የተገኘው ሀገራዊ ለውጥ እንዳይቀለበስ ህዝቡ ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል…ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

66

የካቲት 21/2013 (ኢዜአ ) በብዙ መስዋዕትነት የተገኘው ሀገራዊ ለውጥ ወዳ ኋላ እንዳይቀለበስ ህዝቡ ጠንክሮ ሊሰራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ/ኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስገነዘቡ።

ኢዜማ የምርጫ ዘመቻ ማስጀመሪያ መረሃ ግብሩን ዛሬ በጋምቤላ ከተማ አካሄዷል።

ፕሮፌሰር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በመረሃ ግብር ላይ እንደሉት በጋምቤላ ብሎም በሀገሪቱ በብዙ መሰዋትነትና ጥረት የተገኘውን ለውጥ ወደፊት ለማስቀጠል ህዝቡ ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል።

አሁን ላይ የተፈጠረው ሀገራዊ ለውጥ ሁሉንም የኢትዮጵያዊ እኩልነት የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን በመጠቆም ለውጡን ለመከላከል የሚጥሩ ኃይሎችን ህዝቡ ሊታገለቻው እንደሚገባም ተናግረዋል።

በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት በስርዓቱ አቀንቃኞች ከመዘረፍ ባለፈ ህዝቡን የሚጠቀሙ ብዙ የልማት ስራዎች እንዳልተከናወኑ መታዘባቸውን ጠቁመው ለውጡ ይሄንን የሚያስተካክል መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም ባለፉት ዓመታት በስመ ባለሃብት የክልሉን መሬት በመውሰድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘቦችን በመዝረፍ የራሰቸውን ፍላጎት ከማሟት የዘለ ለህዝቡን የጠቀመ ነገር ያለመኖሩን አስታውቀዋል።

በመሆኑም ከዚህ በኋላ ወደ ክልሉ የሚገቡ ባለሃብቶች እራሳቸውንና ህዝቡን በተጨባጭ የሚጠቅሙ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ከእንግዲህ የህዝቦች አንደነትና እኩልነት የተረጋገጠበት፣ በህዝብ የተመረጠ መንግስት የሚመራበት ጊዜ እንጂ ያለፈው አሰራር የማይመለስበት ወቅት መሆኑን በመግለጽ ህዝቡ ለውጡን ወደ ፊት ለማራመድ የሚሰራበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል።

ኢዜማ ለውጡ የፈጠረውን ምቹ አጋጣሚዎች በመጠቀም የህዝቦች አንደነትና እኩል ተጠቃሚነት የተረጋገጠበት ሀገር እንድትሆን እንደሚሰራም ፕሮፌስሩ ተናግረዋል።

የጋምቤላ ኢዜማ ቅርንጫፍ ኃላፊ አቶ ኡሞድ አግዋ በበኩላቸው ኢዜማ በክልሉ በ6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ብቁ ተፈካካሪ ለመሆን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በመረሃ ግብር ላይ ኢዜማ በክልሉ የሚወዳደሩ እጩዎቹን ለአባላቱ አስተዋውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም