አንድ ሚሊየን ብር ግምት ያለው ሺሻ ሲያዘዋውሩ የነበሩ አሽከርካሪና ረዳቱ ተያዙ

76

አዳማ የካቲት 21 /2013 (ኢዜአ) አንድ ሚሊየን ብር ግምት ያለው ሺሻ ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት የሞከሩ አሽከርካሪና ረዳቱ መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምርያ የኮሚኒኬሽን ሚዲያ ዲቪዥን አባል ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቦቹ የተያዙት ትላንት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ነው።

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3.75494 ኦሮ በሆነና በተለምዶ ዶልፊን የሚል ስያሜ በተሰጠው ተሽከርካሪ 162 ካርቶን የሺሻ አፕል ጭነው ከወሊጪቲ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት ሲሞክሩ መያዛቸውን ተናግረዋል ።

በከተማው ደምበላ ከፍለ ከተማ ኢሬቻ ቀበሌ ልዩ ቦታው ፈጣን መንገድ በተባለ አካባቢ  መያዛቸው የገለጹት ረዳት ኢንስፔክተሯ ፖሊስ አሽከርካሪና እረዳቱን በቁጥጥር ስር  አውሎ ለህግ ለማቅረብ ምርመራ መጀመሩን አስታውቀዋል ።

ህብረተሰቡ ትውልድን የሚያበላሽና ወደ ወንጀል እንዲገቡ የሚያደርግ እፅ  ዝውወር  ለመከላከል ከፖሊስ ጎን እንዲቆም ረዳት ኢንስፔክተሯ  አስገንዝበዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም