ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከ3ሺ 700 በላይ ተማሪዎችን ነገ ያስመርቃል

55

ሐረር ፤የካቲት 19 /2013 (ኢዜአ) ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ3ሺ 700 በላይ ተማሪዎችን ነገ እንደሚያስመርቅ አስታወቀ::

የዩኒቨርሲቲው የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አለምእሸት ተሾመ ለኢዜአ እንደተናገሩት ነገ የሚያስመርቃቸው ተማሪዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩና በተያዘው አመት ያጠናቀቁ ናቸው።

በተቋሙ ዋና ግቢ በሚገኘው ስፖርት አካዳሚ በሚካሄደው ሥነ- ሥርዓት የሚመረቁት ተማሪዎቹ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ መሆኑን አስታውቀዋል።

ዩኒቨርሲቲው ነገ የሚያስመርቃቸው ተማሪዎችን ለ65ኛ ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም