የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአውሮፓ ኅብረትና የጀርመን መንግሥት በጋራ ያበረከቱለትን 22 መኪኖች ተረከበ

59

የካቲት 19 /2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላንትናው ዕለት የአውሮፓ ሕብረትና የጀርመን መንግሥት በጋራ ያበረከቱለትን 22 መኪኖች ተረከበ።

የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በተገኙበት የተፈጸመው ርክክብ 12 ሃርድ ቶፕ እና 10 ፒክ አፕ መኪኖችን ያካተተ ነው።

ዋና ሰብሳቢዋ ቦርዱ የሎጀስቲክ እንቅስቃሴ ላይ ያለበትን ውስንነት ገልጸው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ቦርዱ በመንግሥትም ሆነ በአውሮፓ ሕብረት የሚደረጉለት ድጋፎች አስፈላጊነት ገልጸዋል።


(ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ )

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም