በፊንፊኒ ዙሪያ ልዩ ዞን የትምህርት ቤት ምገባ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

59

የካቲት 19/2013 (ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኒ ዙሪያ ልዩ ዞን 161 ሺህ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የትምህርት ቤት ምገባ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተከናወነ ነው።

በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ የአገልግሎት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይና የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ ተገኝተዋል።

መርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ አስተዳደር ባለፈው ዓመት በዞኑ የተማሪዎች ምገባ ለማስጀመር ቃል በገባው መሰረት ወደ ተግባር መግባቱ ተገልጿል።

የተማሪዎች ምገባው በ669 ሚሊዮን ብር የሚከናወን ሲሆን 161 ሺህ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።

ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን ተጠቃሚ በሚያደርገው የምገባ መርሃ ግብር ተማሪዎቹ የትምህርት ቁሳቁስና ዩኒፎርም እንደሚያገኙም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም