የፌዴራል እና የክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ጉባኤ እየተካሄደ ነው

77

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18/2013 ( ኢዜአ) የሰብዓዊ መብት አያያዝ ማሻሻልን ዓላማ ያደረገው 12ኛው የፌዴራል እና የክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የኮሚሽነሮች ጉባኤ በአዳማ እየተካሄደ ነው።

ጉባኤው በለውጥ መርህ በተቃኘ አስተሳሰብና በሙያዊ ስነ ምግባር በመታገዝ የህግ ታራሚዎችን የሰብአዊ መብት አያያዝ፣ የማረምና የማነፅ አገልግሎትን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ ያለመ ነው ተብሏል፡፡ 

በዚህም "ማረሚያ ቤቶች የህግ ታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች የተከበሩባቸው ተቋማት እንዲሆኑ ተግተን እንሰራለን " በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ ያለው፡፡

የክልልና እና የከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ፤የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ፤ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት ሀላፊዎች በጉባኤው እየተሳተፉ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም