የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ፓርክ ከጉዳት ለመጠበቅ በሚቻልበት ዙሪያ በጂግጅጋ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

67

ጂግጅጋ ፤ የካቲት 18/2013(ኢዜአ) በሱማሌና ኦሮምያ ክልሎች መካከል ያለውን የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ፓርክ ከጉዳት ለመጠበቅ በሚቻልበት ዙሪያ በጂግጅጋ ከተማ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ መጠለያ ፖርኩንና በውስጡ የሚገኙ ዝሆኖቹን ለመጠበቅና ከጉዳት ለመታደግ  በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር በቀጣይ በጋራ ለመስራት ሁለቱ ክልሎች የስምምነት ሰነድ እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፣በምክትል ርዕሰ መሰተዳደር ማዕረግ  የኦሮሚያ ክልል የማህበራዊ ጉዳይ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀሙድ  በምክክር መድረኩ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።


እንዲሁም የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ እና ልማት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመላ ዋቅጅራ፣ የሱማሌና ኦሮሚያ  ተጎራባች አካባቢዎች  አመራር አካላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም  በመድረኩ  እየተካፈሉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም