በኢንጂነር ስመኘው ሞት ጥልቅ ሃዘን ቢሰማንም ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድጋፋችንን እንቀጥላለን-የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

79
አዲስ ኣበባ ሀምሌ 19/11/2010 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ማናጀር ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ዛሬ ጠዋት መስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ሞተው መገኘታቸው ይታዋሳል። አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች በኢንጂኒየር ስመኘው ህልፈተ-ህይወት ጥልቅ ሀዘን የተሰማቸው  መሆኑን ገልጸዋል። ፖሊስ የኢንጂነር ስመኘውን ሞት መንስኤ ምርመራ አጣርቶ በፍጥነት እንዲያሳውቅም ጠይቀዋል። የህዳሴው ግድብ ተጠናቆ የታለመለትን ግብ አንዲመታ ድጋፋቸውን የሚቀጥሉ መሆናቸውንም አስተያየት ሰጪዎቹ ገልፀዋል። ከአስያየት ሰጭዎች  መካከል  አቶ ዳግማዊ ሰለሞን  ኢንጂነር ስመኘውን  ከነበረው ተልዕኮ አንጻር እንደግለሰብ  ስላማላየው  ከባድ ሀዘን  ተሰምቶኛል ብሏል፡፡ ልላኛዋ አስያየት ሰጭ ወይዘሮ  ሂሩት ጓንጉል  በኢንጂነር ስመኘው ሞት በጣም ማዘኗን ገልጻ    ኢንጂነር ስለሞቱ ግድቡ   አይቋረጥም ብላለች፡፡ “የህዳሴ ግድብ  ሲነሳ ኢንጂነሩ ዐይኔ ላይ ድቅን  ይላሉ፣  እኛ ያጣነው አይናችንን ነው። በጣም ትልቅ  ሃዘን ነው የተሰማኝ ለቤተሰቦቹ መጽናናትን እመኛለው እንዲሁም የመላው የኢትዮጵያ ልጅ ነውና ለመላው የአገሪቷ ህዝብ መጽናናትን እመኛሁው”  ወጣት ተውልደ ብርሃን  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም