በአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ

228

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ቀን 2013 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ።

የታሪፍ ማሻሻያው ባለፉት ሁለት ወራት የተደረገውን የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያን ተከትሎ የተደረገ እንደሆነም ተጠቁሟል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ስጦታው አካለ እንዳመለከቱት፤ የታሪፍ ማሻሻያው የመለዋወጫ ዕቃና የጥገና ወጪን ታሳቢ አላደረገም።

በተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ መሰረት የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅና የሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥበት ታሪፍ ባለበት እንዲቀጥል ድጎማ ተደርጓል።

የሚድ ባስ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ታሪፍም እስከ 8 ኪሎ ሜትር ርቀት 3 ብር የነበረው ባለበት ሲቀጥል በሌሎቹ ርቀቶች ላይ ጭማሪ ተደርጓል።

ሚኒባስ ታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ታሪፍ ደግሞ እስከ 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት 2 ብር የነበረው ባለበት ሲቀጥል በሌሎቹ ርቀቶች ከ50 ሳንቲም ጀምሮ እስከ 3 ብር ድረስ የታሪፍ ጭማሪ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም