የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ያስገነባው 14ኛው ትምህርት ቤት በደቡብ ክልል ተመረቀ

95

የካቲት 9/2013 (ኢዜአ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በደቡብ ክልል ከተገነቡት 3 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱን መርቀዋል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በመጀመሪያ ዙር በሁሉም ክልሎች ካስገነባቸዉ 20 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል ከተገነቡት 3 ትምህርት ቤቶች አንዱ የሆነዉንና በጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ ባንቆ ዳዳቱ ቀበሌ ያስገነባዉን ትምህርት ቤት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ መርቀዋል ፡፡

ጽህፈት ቤቱ በክልሉ ያስገነባቸዉ ትምህርት ቤቶች 30 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸዉ ሲሆን በጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ በሽካ ዞን ማሻ ወረዳ እና ደቡብ ኦሞ ዞን ሀመር ወረዳ ይገኛሉ፡፡

ዛሬ የተመረቀዉ ባንቆ ዳዳቱ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቤተ ሙከራ፡ መማሪያ ክፍሎች ፡ቤተ መጽሀፍትና የኮምፒውተር ላብራቶሪ ያካተተ ነዉ፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በደቡብ ክልል በሸካ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ያስገነባቸዉን ቀሪ 2 ትምህርት ቤቶች በቅርቡ እንደሚያስመርቅ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም