የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው

114

ቢሾፍቱ፣ የካቲት 8/2013 ( ኢዜአ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በቢሾፍቱ ውይይት እያካሄደ ነው።

ውይይቱ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ምን ይጠበቃል በሚል እየመከረ ነው።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች አገራዊ ችግሮችን ከመፍታት አንጻር ሚናቸውን እንዴት መወጣት እንዳለባቸው የሚያመላክት እንደሆነም ተገልጿል።

የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት ስራ አስፈጻሚ ወጣት ሜሮን አለሙ ኅብረቱ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርት ከተጀመረ ጀምሮ በአገሪቷ ተከስተው ያለፉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች በእውቀት፣ በጉልበት፣ በገንዘብና በሕይወት መስዋዕትነት ጭምር ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግራለች።

ወረርሽኞች፣ የአንበጣ መንጋና የተፈጥሮ አደጋዎች ሲከሰቱ ከሕዝቡ ጎን በመሆን ሲሰራ መቆየቱንም አስታውሳለች።

እነዚህን መሰል የኅብረቱን ተግባራት አጠናክሮ ለማስቀጠል የውይይት መድረኩ ማስፈለጉንም ገልጻለች።

በውይይቱ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዚዳንቶች ታድመዋል።

ኅብረቱ በውይይቱ ማጠናቀቂያ ቀጣይ ስራዎቹን አስመልክቶ የአቋም መግለጫ እንደሚያወጣ ከመርሃ ግብሩ ማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም