የዱራሜ-ዳንቦያ-አንጋጫ-አመቾ ዋቶ-ሃላባ መንገድ ፕሮጀክት በይፋ ይጀመራል

91

የካቲት 2/2013 (ኢዜአ) የዱራሜ-ዳንቦያ-አንጋጫ-አመቾ ዋቶ-ሃላባ 65 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ይጀመራል።

በተመሳሳይም የሐዌላ-ቱላ ወተራሬሳ-የዩ እና ወንቻ 85 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ይጀመራል።

65 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር ርዝመት ላለው ዱራሜ-ዳንቦያ-አንጋጫ- አመቾ ዋቶ-ሃላባ የመንገድ ፕሮጀክት 1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለታል።

ለሐዌላ-ቱላ ወተራሬሳ-የዩ-ወንቻ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ደግሞ 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ተበጅቶለታል።

የመንገዶቹ ግንባታ ወጪ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የመንገድ ግንባታውን ሲከውን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን ደግሞ በአማካሪነት ይሠራል።

የመንገዶቹ ግንባታው ሶስት ዓመት የሚወስድ ሲሆን እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሮጀክቱ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ይገኛል።

በፕሮጀክቶቹ ማስጀመሪያ መርሃግብር ለመገኘት የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በቦታው ተገኝተዋል።

የመንገድ ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ የሲዳማና የኦሮሚያ ክልሎችን በማስተሳሰር የጎላ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ ይኖራቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም