ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው ሀሰተኛ የሚዲያ ጥቃት አፍሪካ ቀንድን ጭምር ስጋት ላይ የሚጥል ነው... አፍሪካ ኤንድ ዎርልድ

91

ጥር 29/2013(ኢዜአ) ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው ሀሰተኛ የሚዲያ ጥቃት ዘመቻ አፍሪካ ቀንድን ጭምር ስጋት ላይ የሚጥል መሆኑን አፍሪካ ኤንድ ዎርልድ ድረ ገጽ አስነብቧል።

አንዳንድ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በትግራይ ክልል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ እና አሁናዊ የመልሶ ማቋቋም ስራ በተመለከተ የሚያሰራጩት መረጃ ተጨባጭያልሆነ መሆኑን በድረ ገጹ ጽሁፍ ያቀረቡት ላውረንስ ፍሪማን ገልጸዋል።

የህወሃት ቡድን በሰሜን እዝ ላይ ከፈጸመው ክህደት በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ያደረገውን የህግ ማስከበር ዘመቻ መገናኛ ብዙሃኑ ተጨባጭ መረጃ ከማቅረብ ይልቅ ሀሰተኛ መረጃን ለአለም እያሰራጩ ነው ብለዋል፡፡

ይህ ሀሰተኛ የሆነ ከፍተኛ የሚድያ ዘመቻ ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካ ቀንድ ደህንነትንም አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብለዋል።

መንግስት ወደ ጦርነቱ ተገዶ እንዲገባ ያደረገው ገፊ ምክንያት ነበረው ያሉት ጸሃፊው፤ የህወሃት ቡድን የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ መንግስትን በእጅጉ መፈታተኑን ተናግረዋል።

እነዚህ የምዕራቡ አለም መገናኛ ብዙሃን ታድያ የትግራይ ክልል ሁኔታን በተመለከተ የሚያሰራጩት ከእውነት የራቀ መረጃ ነው ያሉ ሲሆን ኢትዮጵያ ድጋፍ እንዳታገኝ የሚያትት ጭምር ነው ብለዋል።

እንደ ዋሽንግተን ፖስት፣ ቢቢሲ፣ ጋርዲያን፣ ኤኤፍ ፒ፣ ለንደን ኢኮኖሚስት እና ሲኤን ኤን የመሳሰሉት የምዕራቡ አለም ሚዲያዎች አሳሳች መረጃ በመልቀቅ የኢትዮጵያን ገጽታን የማጠልሸት ተግባር ፈጽመዋል።እንደ ጸሃፊው ላውረንስ ፍሪማን "ሲኤንኤን በትግራይ ግድያ መፈጸሙን ገልጾ ፤ በማይካድራ ላይ የህወሃት ታማኝ ሀይሎች ከ600 መቶ በላይ በሚሆኑ ንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸሙትን ጭፍጨፋ ለአለም በሚገባ ሳያሳውቅ ቀርቷል" ብለዋል።

"ኤኤፍ ፒ በበኩሉ ተጨባጭ ያልሆነ 4 ነጥበ 5 ሚሊዮን ህዝብ በትግራይ የአስቸካይ ጊዜ እርዳታ ይፈልጋል" በሚል የሀሰት ዘገባ ማስነበቡን አስታውሰዋል።

መገናኛ ብዙሃኑ በትግራይ ክልል ሚሊዮኖች ለረሀብ ስለመዳረጋቸው እና ስለ መሞታቸው፤መንግስት ረሃብን እንደ መሳሪያ ተጠቅሟል፤የጦር ወንጀል ተፈጽሟል በሚል እና የመሳሰሉት ያቀረቧቸው ሀሰተኛ ነበሩ ብለዋል።

መገናኛ ብዙሃኑ የኢትዮጵያ መንግስትን የሚከሱበትን ተደጋጋሚ የሀሰት ዘገባዎች በአለም ዙሪያ ያሉ ሚዲያዎች ተቀባብለውታል ነው ያለው።ላውረንስ ፍሪማን አፍሪካን በተመለከቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትንታኔ የሚሰጡ ምሁር ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም