የአዲስ ወግ ውይይት ‘ኮሙኒኬሽን ለምርጫ ሠላምና ደህንነት’ በሚል ርዕስ እየተካሄደ ነው

1476

አዲስ አበባ፣ ጥር 27/2013 ( ኢዜአ) የአዲስ ወግ ውይይት ‘ኮሙኒኬሽን ለምርጫ ሠላምና ደህንነት’ በሚል ርዕስ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እየተካሄደ ነው።

‘አዲስ ወግ’ በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ትኩረቱን በማድረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በየወሩ የሚካሄድ የውይይት መድረክ ነው።

የዛሬው መድረክም መጪውን ምርጫ ታሳቢ ባደረገ መልኩ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን መምህሯ ዶክተር አጋረደች ጀማነህ፣ የዩኒቨርሲቲው የስነ-ጥበባት ትምህርት ቤት ቤት ዲን ዶክተር ዕዝራ አባተና የኬሚካል ቴክኖሎጂ ባለሙያው ኢንጂነር ጌታሁን ሴራሞ የውይይት መነሻ ፅሁፍ አቅርበዋል።

ፅሁፍ አቅራቢዎቹ ተግባቦቶችና የጥበብ ስራዎች በምርጫ ወቅት ሕዝቦችን በማቀራረብ ለሠላም ግንባታ ሚና መጫወት እንዳለባቸው አመላክተዋል።

በውይይት መድረኩ የመገናኛ ብዙሃን ሃላፊዎችና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል።