በመላው ኦሮሚያ ስለተደረገው የአብሮነት ድጋፍ ድምጽ ከልብ አመሰግናለሁ...ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ

63

ጥር 25 ቀን 2013 (ኢዜአ) “በመላው ኦሮሚያ ስለተደረገው የአብሮነት ድጋፍ ድምጽ ከልብ አመሰግናለሁ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ምስጋና አቀረቡ።

“የመንግስት ልዩ ተልዕኮ ህዝብን ማገልገል ብቻ ነው፤ በየደረጃው ያለን የህዝብ አገልጋዮች ከእንደዚህ አይነት ድጋፍ የምንማረው እና መገንዘብ ያለብን ሀላፊነታችንን በአግባቡ እንድንወጣ የህዝብ ጥሪና አደራ እንዳለብን ሊሆን ይገባል” ብለዋል።

“ዛሬ ለታየው እና ለነበረው ሰፊ ንቅናቄ መላው የኦሮሚያ ክልል ነዋሪን ከልብ አመሰግናለሁ” ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስነብበዋል።

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች እየተከናወነ ላለው የለውጥ ተግባርና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ አስተዳደር ድጋፍ ለመስጠት ዛሬ ሰልፍ መካሄዱ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም