አምቦ፣ ቦንጋ እና መቱ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን እያስመረቁ ነው

78

አምቦ/ቦንጋ/መቱ፤ ጥር 22/2013 (ኢዜአ)  አምቦ ፣ቦንጋ እና መቱ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠኗቸውን ተማሪዎችን እያስመረቁ ነው፡፡

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሲያሰመርቅ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

አምቦ  ዩኒቨርሲቲ  እያሰመረቃቸው ያሉት ተማሪዎች  ከ5ሺህ በላይ ሲሆኑ  የሠለጠኑትም በመጀመሪያ ፣ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ  መሆኑን በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

ለተመራቂዎቹ በኮሮና ክስተት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት በማካካስ እንደተሰጣቸው እና ከተመራቂዎቹ መካከል 1ሺህ 810 ሴቶች መሆናቸው ተመልክቷል።

የምረቃው ሥነ-ሥነ-ሥርዓት በዩኒቨርሲቲው ሥር ባሉ ሃጫሉ፣ ጉደር ማሞ መዘምር፣ ወሊሶ ካምፓስና ዋናው ግቢ የሚያጠቃልል ነው።


በተመሳሳይ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ  ለመጀመሪያ ጊዜ 827 ተማሪዎችን  እያስመረቀ ይገኛል።


ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ የሰለጠኑ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት የሚያስተምራቸው 6ሺህ 348 ተማሪዎች እንዳሉት ተመልክቷል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ መቱ ዩኒቨርሲቲ ለሰባተኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ  ነው።

በሶስቱም ዩኒቨርሲቲዎች እየተካሄደ ባለው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት  የፌደራልና ክልል  ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ሃላፊዎች  እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች መገኘታቸውን በሥፍራዎቹ የሚገኙት ሪፖርተሮቻችን ዘግበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም