የኢትዮ-ቴሌኮም የስራ ሃላፊዎች በገበታ ለአገር የሚለማውን የወንጪ ፕሮጀክትን እየጎበኙ ነው

64

ጥር 21/2013(ኢዜአ) የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በገበታ ለአገር የሚለማውን የወንጪ ፕሮጀክት እየጎበኙ ነው።

የስራ ሃላፊዎቹ ጉብኝት በዋናነት ቴሌኮሙ በፕሮጀክቱ የሚያከናውነውን ስራ በተመለከተ የመስክ ምልከታ ለማድረግ ነው።

ኢትዮ-ቴሌኮም በፕሮጀክቱ ከሚያከናውነው ስራ በተጨማሪ ለገበታ ለአገር ፕሮጀክቶች 500 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም