ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ በፍርድ ቤቶች የስራ ጉብኝት ለማድረግ ባህር ዳር ገቡ

158

ባህር ዳር ጥር 21 /2013 (ኢዜአ) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ በፍርድ ቤቶች የስራ ጉብኝት ለማድረግ ባህርዳር ገቡ።

ፕሬዝዳንቷ በአንድ ቀን የባህር ዳር ቆይታቸው በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና በባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመገኘት የሰበር፣ የወንጀልና የፍታብሄር እንዲሁም የሬጅስትራር የስራ እንቅስቃሴን ይመለከታሉ።

ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ ከማኔጅመንት አባላት፣ ከጉባኤ ተሿሚዎችና ሂደት አስተባባሪዎች ጋር በፍትህ ሰጣጥና አጠቃላይ አሰራሮች ላይ ውይይት ያካሂዳሉ።

ፕሬዝዳንቷ ከክልሉ ርእሰ መስተዳደርና አፈ ጉባኤ ጋርም እንደሚወያዩ ከመርሀ ግብሩ ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም