በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በዱብቲ ከተማ የተገነባ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ይመረቃል

56

ሰመራ፣ ጥር 20/ 2013 (ኢዜአ) በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በአፋር ክልል አውሲ-ረሱ ዞን ዱብቲ ከተማ በ13 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ይመረቃል።

በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፣ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ጨምሮ የፌደራልና የክልሉ ባለስልጣናትና የስራ ሀላፊዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

ትምህርት ቤቱ በሁለት ፈረቃ 1ሺህ 800 ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተናገድ አቅም እንዳለው ተነግሯል።

ትምህርት ቤቱ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ- ሙከራ፣ ቤተ-መጻህፍትና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎች የተሟሉለት መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም