የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ 4 ሺህ 858 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ 4 ሺህ 858 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው
56
አርባምንጭ፣ ጥር 18/2013 (ኢዜአ) የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ33ኛ ጊዜ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 4ሺህ 858 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው ።
ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት የሚያስመርቃቸው ተማሪዎች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ደረጃ ለአንድ ወር የተሰጣቸውን የማካካሻ ትምህርት በአግባቡ ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተነግሯል ።
ከተመራቂዎች መካከል 1ሺህ 717ቱ ሴቶች ናቸው።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ተገኝተዋል።