በኦሮሚያ ክልል የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ

87

አዳማ፣  ጥር 17/2013( ኢዜአ) በአሮሚያ ክልል የትራንስፖርት ቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ገለጸ።

በክልሉ  በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት  የዘርፉ  እቅድ  አፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ከተማ በተካሄደበት ወቅት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብድልቃድር ሁሴን  የመንገድ ትራፊክ አደጋ በተደጋጋሚ እንደ ክልላችን ከፍተኛ ነበረ ብለዋል።

የትራንስፖርት ቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት ከዞን፣ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከሚመለከታቸው አስፈፃሚዎች ጋር  በቅንጅት በመስራት ለውጥ መታየቱን ገልጸዋል።

አደጋውን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ በማስቀጠል  የመንገድ ደህንነት እቅድ ግቡን እንደሚመታ የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ውጤት  ከማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

በባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ ተፈሪ መኮንን በበኩላቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅተው በመሥራት የሞትና ንብረት ውድመትን ባለፈው ዓመት ከነበረው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ4 ነጥብ 6 በመቶ መቀነሱን ተናግረዋል።

የባለፈው ግማሽ የበጀት ዓመት የአደጋ ብዛት 664 ፤  የዘንድሮ ተመሳሳይ ወቅት ግን 636 እንደሆነ ጠቅሰዋል።

የሞት አደጋ ባለፈው ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ  829 የዘንደሮው ገን  783 ፣ የንብረት ውድመትም መቀነሱን  አመላክተዋል።

የትራፊክ መንገድ ቁጥጥሩን በማጥበቅ  በ45 ቀኑ ውስጥ ብቻ የትራፊክ ደንብን የተላለፉ ከ14 ሺህ በሚበልጡ  አሽከርካሪዎች ላይ የማስተካከያ  እርምጃ መወሰዱን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም