በዛሬው የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ድሬድዋ አዳማን 3 ለ 0 አሸነፈ

1568

ጅማ፣ ጥር 17/ 2013 (ኢዜአ) ዛሬ ጧት 4 ሰዓት ላይ በተካሄደው ዘጠነኛው ሳምንት የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬድዋ ከተማ አዳማ ከተማን 3 ለ 0 አሸነፈ፡፡

ሙህዲን ሙሳ በ15ኛዉና በ24ኛዉ ደቂቃ እንዲሁም አስቻለዉ ግርማ በ48ኛዉ ደቂቃ ለድሬድዋ ከተማ 3 ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡

ድሬድዋ ከተማ አዳማን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፏል፡፡

ድሬዎች በዛሬዉ ጨዋታ ሶስት ነጥብ በማግኘት ባጠቃላይ 10 ነጥብ በመሰብሰብ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

ከሰአት ሀዲያ ሆሳዕና ከሀዋሳ ከነማ ተጫዉተዉ የፕሪሚየር ሊጉ የዘጠነኛዉ ሳምንት መርሀግብር ይጠናቀቃል፡፡