የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በድሬዳዋ ተጀመረ

88

ድሬዳዋ ጥር 16 /2013 (ኢዜአ) 8ተኛው የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፕሪሚየር ሊግ 1ኛ ዙር የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ በድሬዳዋ ተጀመረ ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻኪር አህመድ ውድድሩን አስጀምረዋል ።

ከዛሬ ጥር 16 እስከ 22 ቀን 2013 ዓም በሚቆየው  ውድድር አምስት  የወንድና  አምስት  የሴት ክለቦች ይሳተፋሉ።

በአማራ መንገድና ህንጻ ዲዛይንና በሀዋሳ ከተማ ሴቶች ቡድን መካከል በሚደረግ ጨዋታ የመክፈቻ ውድድሩ ተጀምሯል ።

የጅማና ወልቂጤ ከተማ የሴት ቡድኖ እንዲሁም በወንዶች ወልቂጤ ከሀዋሳ ከተማና ድሬዳዋ  ከጎንደር ከተማ በዛሬው እለት እንደሚጫወቱ ታውቋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም