በሊጉ ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና አሸነፉ

58

ጅማ፣ጥር 13/ 2013 (ኢዜአ) በጅማ ዛሬ በተካሄደው ስምንተኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና ድሬድዋ ከተማን አንድ ለዜሮ ሲረታ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ጅማ አባጅፋርን ሶሰት ለአንድ አሸነፈ፡፡

በጥዋቱ የጨዋታ መርሀግብር ሳሊፋ ፎፋኖ ባስቀጠራት ብቸኛ ግብ ሀዲያ ሆሳዕና በድል አጠናቋል፡፡

ቡድኑ በጠባብ ልዩነት በማሸነፍ ባገኘው ሶሰት ነጥብ  ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ማለት ችሏል፡፡

ከሰዓት ቦኋላ በተደረገው  ጨዋታ የቡናው  አቡበከር በ22ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል በመምራት እረፍት ሆኗል፡፡

ከእረፍት መልስ  በ65ኛው ደቂቃ ቡዛየሁ እንደሻው ለጅማ አባጅፋር ቢያስቆጥርም አስራት በ81ኛው ደቂቃ እና ዊሊያም በ87ኛው ደቂቃ ግቦች በማስቆጠሯቸው  ቡና ሶሰት ለአንድ አሸንፎ መውጣት ችሏል፡፡

የአባጅፋር ዋና አሰልጣኝ ጳውሎስ ማንጎ ከአሰልጣኝነታቸው በመነሳታቸው  በምክትል አሰልጣኙ አማካይነት ነው ቡድኑ  የዛሬውን ጨዋታ ያካሄደው፡፡

የፕሪሜር ሊጉ የስምንተኛ ሳምንት የጨዋታ መርሀግብርም በዚሁ ተጠናቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም