ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ

119

አዲስ አበባ፣ ጥር 13 ቀን 2013 (ኢዜአ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቦርድ አባላት ሹመትን መርምሮ አጸደቀ፡፡

በዚህም መሰረትም 1. ዶክተር አብርሃም በላይ - ሰብሳቢ

2. ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ - አባል

3. አቶ ጣሂር መሐመድ - አባል

4. ረዳት ፕሮፌሰር መኩሪያ መካሻ - አባል

5. ወይዘሮ ሰሃርላ አብዱላሂ - አባል

6. አቶ አብነት ዘርፉ - አባል

7. አቶ ሰይፈ ደርቤ - አባልና ፀሀፊ ሆነው በሙሉ ድምፅ በምክር ቤቱ ተሹመዋል፡፡

የቦርድ አባላቱ ሹመት ኢዜአ ተልዕኮውን በተሻለ ሁኔታ በብቃት ለመወጣትና ስራዎቹን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚያግዘው ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሆኖ በአዋጅ ቁጥር 1115/2011 እንደገና መቋቋሙ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም