የጁንታውን ታጣቂ ሃይል በመምራትና በማዋጋት የተሳተፉ የቀድሞ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች እጃቸውን ሰጡ

96

ወንጀለኞችን የማደን እና ለህግ የማቅረብ ዘመቻው ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸው፤ ቀሪው የጁንታው ቡድን አባላት ህይወታቸውን ለማትረፍ በዋሻ እና ገደል እየተሹልከለኩ ነው ብለዋል።

የአገር መከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ የተቀናጀ ወንጀሎኞችን የማደን ተግባር መቀጠሉን ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች የነበሩ እና  በጡረታ ተሰናብተው ከጁንታው ጋር በመቀላቀል  አመራር ሲሰጡ የነበሩ ጄኔራል መኮንኖች በትናትናው ዕለት ለአገር መከላከያ ሰራዊት እና በቀጠናው ለሚገኘው ፌዴራል ፖሊስ እጅ እንደሰጡ ሜጄር ጀኔራል መሐመድ ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት :

1ኛ የቀድሞ የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ የነበሩ በኋላ ላይ  የዘመቻ መምሪያ ሃላፊ የነበሩ እና በጡረታ የተሰናበቱ ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ  እጃቸውን ሰጥተዋል።

2ኛ በምስራቅ ዕዝ የዕዝ ኮማንድ የነበሩ እና በጡረታ የተሰናበቱ ብርጋዴል ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ እጃቸውን ሰጥተዋል።

በርካታ የጁንታው ቡድን ልዩ ሃይል፤ የሚልሻ እና  ፖሊስ አባል የነበሩ በተለያዩ አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ ለአገር መከላከያ ሰራዊት እጃቸውን በመስጠት ህጋዊ ከለላ እየተሰጣቸው ይገኛል ብለዋል።

ሙሉ በሙሉ የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ስር እስከሚውሉ ድረስ ዘመቻው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

ህዝብን ለማደናገር በማህበራዊ ሚዲያዎች የጁንታው ቡድን ይመጣል  በሚል የሚነዙ ወሬዎች ማደናገሪያ ሃሳቦች መሆናቸውን ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ገልጸዋል።

የጁንታው ቡድን ከዚህ በኋላ በዋለበት ማደር የማይችል እንደሆነም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም