በ8ኛው ሳምንት የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨቃታ በህርዳር ከተማና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

82

ጅማ፣ ጥር 12/ 2013 (ኢዜአ) ትናንት በተካሄደው ስምንተኛው ሳምንት የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በህርዳር ከተማ ሰበታ ከተማን 4 ለ 1 ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ዲቻን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በ4 ሰአቱ ጨዋታ ከዕረፍት በፊት ሰበታዎች በ43ኛው ደቂቃ ፍጹም ገብረማርያም ባስቆጠራት ግብ መምራት ችለው ነበር፡፡

ከዕረፍት በኋላ በ51ኛው ደቂቃ  የባህር ዳሩ ያሬድ ሀሰን ቡድኖቹን አቻ የምታደርገውን የመጀመሪያውን ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡

በ68ኛው ደቂቃ ሳለአምላክ ተገኝ ሁለተኛዋን ጎል በማስቆጠር ባህርዳር መሪነቱን መያዝ ችሏል፡፡

በ76ኛው ደቂቃ ምንይሉ ወንድሙ ሶስተኛዋን ግብ ለባህር ዳር አስቆጥሯል፡፡

90 ደቂቃ አልቆ በተሰጠው የባከነ ሰአት በ5ኛው ደቂቃ መሳይ ጳዉሎስ በምንይሉ ላይ በሰራው ጥፋት ፍጹም ቅጣት ምት ለባህርዳር ተሰጥቶ ግርማ ዲሳሳ ለቡድኑ አራተኛውን ግብ አስቆጥሯል፡፡

ባህርዳር ከተማ በከፍተኛ የግብ ልዩነት 4ለ1 አሸንፎ ደረጃውን ወደ 2ተኛ ከፍ አድርጓል፡፡

በሌላ በኩል ዘጠኝ ሰአት ላይ በተደረገው ጨዋታ ሳላዲን ሰኢድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ በ83ኛው ደቂቃ ላይ ግብ በማቆጠር ወላይታ ዲቻን አሸንፏል፡፡

በፕሪምርሊጉ የጎል አስቆጣሪ ሰንጠረዥ ሙጂብ ቃሲም በዘጠኝ ጎል ፣ አቡበከር ናሲር በስምንት ጎል እና ጌታነህ ከበደ በሰባት ጎል ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም