የደቡብ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ሰባተኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ

63
ሀዋሳ ሀምሌ 17/2010 የደቡብ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አምስተኛ ዙር ሶስተኛ የስራ ዘመን ሰባተኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተጀመረ፡፡ አሁን የተጀመረው ይሄው መረሃ ግብር የአምስተኛው ዙር ስድስተኛ   መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ቀርቦ  ምክር ቤቱ ከተወያየበት በኋላ እንደሚጸድቅ ተመልክቷል፡፡ ለአንድ ቀን በሚካሄደው የምክር ቤቱ ጉባኤ ሹመቶችና የ2011 የስራ ዘመን ማስፈጸሚያ በጀት እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል፡፡                    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም