በጎንደር የከተራ በዓል ባህላዊና ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ ተከብሯል --ታዳሚዎችና የኅይማኖት አባቶች

86

ባህር ዳር ጥር 11/2013 (ኢዜአ) በጎንደር የከተራ በዓል ባህላዊና ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ መከበሩን የበዓሉ ታዳሚዎችና የሃይማኖት አባቶች ገለፁ።

በጎንደር ከተማ የከተራ በዓል ትላንት በድምቀት ተክብሯል።

በበዓሉ የተገኙ የማልዕከላዊ ጎንደር ሃገር ስብከት ስራ አስኪያጅ ሊቀ ህሩያን አባዮሴፍ ደስታ ለኢዜአ እንዳሉት የጥምቀት በዓል ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች የነፃነትና የደህንነት በዓል ነው።

የጥምቀት በዓል ከቀደሙ አባቶች ጅመሮ ሃይማኖታዊም ሆነ ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ በድምቀት የሚከበር በዓል እንደሆነ ገልፀዋል።

የጥምቀት ስነ ስርዓቱ በአዔ ፋሲል የጥምቀተ ባህር በየዓመቱ በድምቀት እንደሚከበር ጠቁመው "የዘንድሮ በዓል ከዚህ ቀደም ከነበረው የደመቀና የሞቀ ነው" ብለዋል።

በበዓሉ ቤተክርስቲያኗም ሆነች መንግስት ሰፊ ዝግጅት በማድረጋቸው በሰላማዊ መንግድ ስርዓት ይዞ እየተከበረ መሆኑን አመልክተዋል።

በጥምቀተ በዓሉ ለመታደም ከጎንደር የመጣው አለሜ ነው ተስፋ በበኩሉ "የጥምቀት በዓል የጎንደርና አካበባቢው የጥንት መገለጫ ነው" ብሏል።

ከዚህ ቀደም በጥምቀት በዓል የታደመ ቢሆንም እንደ ዘንደሮ የደመቀ እንዳልነበር ገልጻል።

"የጥምቀት በዓል በመላ ሃገሪቱ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበር በዓል ቢሆንም በጎንደር የተለየ ነው" ብሏል።

"በጎንደር የጥምቀት በዓል ከድራሩ ጀምሮ የጥንት ባህሉን በጠበቀ መንገድ በባህላዊ አልባሳትና የጸጉር ስሬት በመድመቅ ኢትዮጰያዊነትን በሚያጎላ መንገድ እየተከበረ ነው" ሲል ገልጻል።

"የጥምቀት በዓል በየዓመቱ የሚከበር ቢሆንም የዚህ ዓመት ከዚህ በፊት ከነበረው ላቅ ያለና ደማቅ ነው" ያለችው ደግሞ  የከጎንደር ከተማ ነዋሪ ሰናይት ያለውለት ነች።

በጥምቀት ስነ ስርዓቱም ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የመጡ ዜጎች መታደማቸውን ገልፃለች።

ባህላዊ ቱሁፊቱ እንዳይጠፋም ከአባቶችና እናቶች የመጣው ባህልን የማክበር ልምድ በጠነከረ አግባብ እንዲቀጥል የበኩሏን እንደምትውጣ አስያውቃለች።

"የዘንድሮ የከተራ በዓል ይማኖታዊና ባህልዊ አካሄዱን ጠብቆ እየተከበረ ነው" ያሉት ደግሞ የከተማው ነዋሪ አቶ ዮሐንስ አዲሱ ናቸው።

በጎንደር ከተማ የከተራ በዓል በደመቀ ሁኔታ ማምሻውን ፅላተ ታቦቱን ከመንገሻው ማደሪያ አፄ ፋሲል ጥምቀተ ባህር ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቱን ጠብቆ ተከብሯል።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም