ጥምቀት ከመለያየት፣ ቂምና ጥላቻ የምንፈወስበት ሊሆን ይገባል - ብፁዕ ዶክተር አቡነ አረጋዊ

261

ጥር 11/2013 (ኢዜአ) ጥምቀት ከመለያየት፣ ቂምና ጥላቻ የምንፈወስበት ሊሆን ይገባል ሲሉ የፓትሪያርኩ ልዩ ጽህፈት ቤትና የውጭ ጉዳይ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ ዶክተር አቡነ አረጋዊ ተናገሩ።

በአዲስ አበባ የሚገኙ አድባራትና ገዳማት ታቦታት ወደ ባሽሕረ ጥመቀት የወረዱ ሲሆን ምዕመናኑ በእልልታና በሆታ፤ ካህናቱ በአኮቴት (ምስጋና) እና ሽብሸባ ሽኝት አደርገዋል።

በአዲስ አበባው የጃንሜዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብጹዕ አቡነ ማትያስን ጨምሮ ብፁዓን አባቶችና እንግዶች በታደሙበት ተከብሯል።

የፓትሪያርኩ ልዩ ጽህፈት ቤትና የውጭ ጉዳይ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ ዶክተር አቡነ አረጋዊ በዓል ጥምቀት እየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ሐጥያት ያነጻበት፣ የአዳምን የእዳ ደብዳቤ የተቀደደበት ለዚህም በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ተጠምቆ ትህትናውን ያሳያበት ዕለት እንደሆነ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው አበይት በዓላት አንዱ የሆነው ጥምቀትም ታቦታት ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባህር የሚወርዱት ይህንኑ ለማሰብ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ከኢየሩሳሌም ቀጥሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በተጠመቀው በኢትዮጵያዊ ጃንደረባው ጥምቀት መጀመሯን፣ ጥምቀት ማክበር የጀመረችውም በ4ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይገልጻሉ።

ጥመቀት ከመንፈሳዊ ፋይዳው ባሻገር ኢትዮጵያዊነት የሚታይበት ማህበሰራዊ እሴቱ የጎላ በ'ዓል እንደሆነም ተናግረዋል።

ጥምቀት እየሱስ ክርስቶስ የእዳ ደብዳቤ የቀደደበት ዕለት በመሆኑ እኛም ከጥላቻ፣ በቀልና ግጭት በመራቅ ከእኩይ ድርጊቶች በመቆጠብ ልናከብር ይገባል ብለዋል።

በዓሉም ከሁከትና ከጥላቻ የእዳ ደብዳቤ የሚወገድበት እንዲሆን ተመኝተዋል።

የገነተ ጽጌ ጊዮርገፊስ የቅዳሴ መምህረሩ ተክሌ ገብረእግዚአብሄር እንዳሉትም በዓሉ የሰው ልጆች ሁሉ የፍቅርና አብሮነት ተምሳሌት በመሆኑን አብራርተዋለ።

ጥምቀት በወርኃ ጥር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በአደባባዮች በድምቀት ተከብሮ የሚውል ኃይማኖታዊ በዓል ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም