ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎቹን ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ነው

84

ጥር 10/2013(ኢዜአ) ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስክች ያሰለጠናቸውን  ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ቶፊክ ጀማል ለኢዜአ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ጥር 15 ቀን 2013 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ 850 ተማሪዎችን ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የመማር ማስተማር ሂደት ለወራት ተቋርጦ መቆየቱን ያስታወሱት ዶክተር ቶፊክ፤በመንግስት አቅጣጫ መሰረት የሶስተኛ ዓመት ተመራቂ ተማሪዎችን የማስተማሩ ስራ መቀጠሉን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው የሚያስመርቃቸው በአራት ኮሌጆች በ14 የትምህርት ክፍሎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎችን እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማሩ ስራ በተጨማሪ የማኅበረስብ አግልግሎትና የምርምር ስራዎችን በመስራት የአካባቢውን ነዋሪዎች እየደገፈ መሆኑንም ገልፀዋል።

በተለይም በማኅበረሰብ አገልግሎት በመስጠት ወደ ማኅበረሰቡ ለመድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነው የተናገሩት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም