በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ ከአራት ሺህ 600 በላይ ተተኳሽ ጥይት በቁጥጥር ሥር ዋለ

141

ደሴ ፣ ጥር 10/2013 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ በህገ ወጥ መንገድ ለማዘዋወር ሲሞከር የተገኘ ከአራት ሺህ 600 በላይ ተተኳሽ የክላሽንኮቭ ጥይት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ፡፡ 

የቅርንጫፉ ደንበኞች ትምህርት ቡድን አስተባባሪ አቶ አሳምነው አዳነ ለኢዜአ እንደገለጹት ጥይቱ በቁጥጥር ሥር የዋለው ትናንት ሌሊት በታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3 - 98355 አዲስ አበባ በሆነ የጭነት አይሱዙ ተሸከርካሪ በሰዎች ተጭኖ ከመቀሌ ወደ ባህርዳር ለመጓዝ ሲሞክሩ ወልድያ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ ነው ፡፡

የጉምሩክ ሠራተኞች፤ የፌደራልና ክልል ፖሊሶች ባደረጉት ቅንጅታዊ ጥረት ከጉዳዩ ጋር የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች ጭምር በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡

በአካባቢው እየተስፋፋ የመጣውን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር እና ኮንትሮባድ ንግድ ለመከላከል ህብረተሰቡ የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በቅርቡም 11 ሺህ የሚጠጋ የተለያየ ተተኳሽ ጥይት በህገ ወጥ መንገድ በሰዎች  ሲጓጓዝ በቅርንጫፉ መስሪያ ቤቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን በወቅቱ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም