በአምባሰል ወረዳ በ64 ሚሊዮን ብር ወጭ የተገነባ የመስኖ ፕሮጀክት ተመረቀ

61

ደሴ፤ጥር 6/2013 (ኢዜአ)በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ በ64 ሚሊዮን ብር ወጭ የተገነባ የላይኛው ሚሌ መስኖ ፕሮጀክት ተመርቆ አገልግሎት ጀመረ።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደርና  የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ተገኝተዋል።

የክልሉ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኅላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው በወቅቱ እንደገለጹት፤የመስኖ ፕሮጀክቱ 6 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የውሀ መውረጃ ቦይ የተገነባለትና 350 ሄክታር መሬት የማልት አቅም ያለው ነው።

ፕሮጀክቱ 750 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በዛሬው እለት የተመረቀው ፕሮጀክቱ  በመስኖ ልማት ስልጠና በተሰጣቸው አርሶ አደሮች ስራ እንዲጀምር መደረጉን አስታውቀዋል።

በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት 2 ሺህ 955 ሄክታር መሬት ማልማት የሚችሉ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን፤ም ኅላፊው አስታውቀዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገርና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ዛሬ ከቀትር በኋላም የይስማ ንጉስ ሙዚየምና 40 ሜትር ርዝመት ያለውን የአጅማ ድልድይ ይመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም