ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ከ1ሺህ 200 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

1546

ፍቼ፤ ጥር 6/2013(ኢዜአ) ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛው ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸው ከ1ሺህ 200 በላይ ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው በአምስት ኮሌጆቹ በመጀመሪያ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ምረቃቸው ዘግይቶ እንደነበር ተገልጿል።

ዛሬ የተመረቁት ተማሪዎች በግብርናና ተፈጥሮ ሀብት፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በጤና ሳይንስ ኮሌጆች የሠለጠኑ መሆናቸው ተመልክቷል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 555 ሴቶች እና 711 ወንዶች ሲሆኑ በሥነ-ሥርዓቱ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።