በአማራ ክልል የበጋ ወራት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ተጀመረ

71

ባህር ዳር ፣ ጥር 4/2013( ኢዜአ) በአማራ ክልል የዘንድሮው ወራት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ዛሬ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ላይ አርማጭሆ ወረዳ ተጀመረ። 

ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር በተገኙበት ክልላዊ የበጋ ወራት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ የተጀመረው በወረዳው ችራ ቀበሌ በሶኒ ተፋሰስ ህዝቡን በማሳተፍ ነው።

በሥነ-ሥርዓቱ  የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሳኒ ረዲ ጨምሮ ሌሎች የፌደራል፣ ክልልና ዞን ከፍተኛ አመራሮችም  ተገኝተዋል።

በዘንድሮው የበጋ ወራት ከ8 ሺህ 300 በሚበልጡ ተፋሰሶች ውስጥ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ እንደሚከናወን  የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልጿል።

በተፋሰሶቹ  ውስጥ  ከ328 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ የተጎዳ መሬት ላይ ልማቱ እንደሚካሄድ ተመልክቷል።

ለሁለት ወራት በሚቆየው በዚሁ ሥራ ከአራት ሚሊዮን 600 ሺህ  በላይ ህዝብ  እንደሚሳተፍ የሚጠበቅ መሆኑን የግብርና ቢሮ አስታውቋል።

ለልማት ስራው የሚያግዙ አካፋ፣ ዶማና ሌሎችም ቀላል የእጅ መሳሪያዎች መዘጋጀታቸውም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም