በአሜሪካ ካፒቶል የተፈጸመው ድርጊት ለዴሞክራሲ ‘የማንቂያ ደውል ነው’ -የአውሮፓ ህብረት

106

ጥር 03/2013 (ኢዜአ) ባለፈው ሣምንት በአሜሪካ በካፒቶል ሂል የተፈጸመው ረብሽ ለዴሞክራሲ መብት ተሟጋቾች ‘የማንቂያ ደውል ነው’ ሲሉ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ተናገሩ፡፡

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት ቅስቀሳ ምክንያት አክራሪ ደጋፊዎቻቸው በአሜሪካ በካፒቶል ሂል የመሰብሰቢያ አዳራሽ አመጽ በመቀስቀሳቸውና የአምስት ሰዎች ሕይዎት ያለፈ ሲሆን ድርጊቱ በበርካቶች ዘንድ ተቃውሞ እያስተናገደ ይገኛል፡፡

በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ  ያልተረጋገጡና  ምንጫቸው ያልታወቁ የሀሰት መረጃዎች እንዲለቀቁ መፈቀዱ

ለዴሞክራሲ ዕሴቶቸ መሸርሸር ምክንያት መሆናቸውንም በአሜሪካ ካፒቶል የተፈጸመው ከበባ አንዱ ማሳያ መሆኑን ሃላፊዋ ገልጸዋል፡፡

ድርጊቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ ክስተቶች እየተበራከቱ መምጣታቸው ለዲሞክራሲ ተሟጋቾች የማንቂያ ደወል መሆን አለበት ሲሉ መናገራቸውን ኤስ ኤ ቢሲ ኒውስ ዘግቧል።

የዴሞክራሲ ባህልን የሚጎትቱ ድርጊቶችን ሁሉም በትኩረት ሊታገላቸውና ሊያወግዝ  ይገባል ያሉት ኃላፊዋ መሰል ድርጊቶችን ሁሉም በሚገባ ካልተከታተለውም ለዴሞክራሲ ዕሴቶችና ተቋማት አደጋው የከፋ ነው ብለዋል፡፡

አሜሪካውያን ከፕሬዝደንታዊ ምርጫው ውጤት ጋር በተያያዘ ጥርጣሬና ስጋት ቢኖርባቸውም እንኳን ዴሞክራሲያዊ መንገድን ተከትለው ሊጠይቁ  እንደሚገባም  ተናግረዋል።

ለድርጊቱ ያበቃውን መረጃ ከመመርመር ባለፈም ተቋማቱ ራሳቸው ሊፈተሹ ይገባል ሲሉ ኃላፊዋ አክለው ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በተደጋጋሚ በሚለቋቸው ኃላፊነት ጎደላቸው መረጃዎች ከዘጠና ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለውን የትዊተር ገጻቸውን መዘጋቱ ይተዋሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም