የጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክርቤት አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክርቤት አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
66
ጋምቤላ፣ ጥር 2 ቀን 2013 (ኢዜአ) የጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ዛሬ ተጀመረ።
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ጁል ናንጋል በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፤ በክልሉ ብሎም በአገር ደረጃ እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል።
በተለይም የምክር ቤቱ አባላትና በየደረጃው የሚገኘው አመራር የላቀ ድርሻ እንዳለባቸውም አስገንዘበዋል።
"ዘንድሮ የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን ሁሉም አበከሮ ሊሰራ ይገባል" ብለዋል።
በክልሉ ያለውን ሰላም በማጠናከር የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ውጤታማ ለማደረግ መትጋት እንደሚገባም አመላክተዋል።
ጉባኤው በሚኖረው የአንድ ቀን ቆይታ በክልሉ በየእርከኑ የሚገኙ የምክር ቤቱ አባላት የህዝብ ተወካዮችን ብዛት ለመወሰን የወጣን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።