ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ከጦር አካል ጉዳተኞች ጋር የገና በአልን እያከበሩ ነው

68

አዲስ አበባ ታህሳስ 29/2013 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሚኒስትሮችና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ከጦር አካል ጉዳተኞች ጋር የገና በአልን እያከበሩ ነው።

በአገር መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና በአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በትብብር ባዘጋጁት በጋራ በዓል የማክበር ስነ-ስርዓት ላይ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል።

ልደታ በሚገኘው የአካል ጉዳተኞች ተሀድሶ ማእከል በሚከበረው በዓል ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ እና የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም