የአምራች ኢንዱስትሪውን የሚያግዝ የ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ብድር ተገኘ

168

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13/2013 ( ኢዜአ) የአምራች ኢንዱስትሪውን የፋይናንስ እጥረት ለመፍታት የሚያስችል የ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ብድር ከአለም ባንክ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።

ሚኒስትሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ገንዘቡ ለሊዝ ፋይናንሰ፣ ለፕሮጀክት ፋይናንስና ለስራ ማስኬጃ እንደሚውል አረጋግጠዋል።

ዘርፉን ከሚያጋጥሙት ችግሮች መካከል አንዱ የፋይናንስና  የውጭ ምንዛሬ እጥረት መሆኑን ጠቅሰው ከዓለም ባንክ የተገኘው የ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ችግሩን ለማቃለል ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።

ከአለም ባንክ የተገኘው ብድር 1 ሺህ 990 ነባር ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም አዲስ ለሚቋቋሙ ኢንዱስትሪዎች የሚደርስ መሆኑንም አቶ መላኩ አመልክተዋል።

የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በሁሉም አካባቢ እንዲደርስ ከማድረግ አንጻር ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑንም አብራርተዋል።

በቀጣይም ሌሎች የዘርፉ ማነቆዎችን ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም