ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የማበረታታትና ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ መርሃግብር ይፋ ሆነ

76

አዲስ አበባ ታህሳስ 12/2013 (ኢዜአ) ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለማብቃት፣ ለማበረታታትና ስኬታማ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚረዳ መርሃግብር ይፋ ሆነ።

መርሃግብሩ ይፋ የሆነው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዝዳንት መአዛ አሸናፊን ጨምሮ ከፍተኛ ሴት አመራሮችና ሚኒስትሮች በተገኙበት ነው።

መርሃ ግብሩ ትኩረት ያደረገው በ2013 የትምህርት ዘመን ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ያሉ  ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ነው።

በዚህም መሰረት የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ 50 ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመርሃግብሩ ተካተዋል።

መርሃግብሩ አማካኝነትም በተሰማሩበት የስራ መስክ ስኬታማ የሆኑ ሴቶች እያንዳንዳቸው አንድ ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪን በምክር፣ በማበረታታትና ልምድን በማካፈል እገዛ የሚያደርጉ ይሆናል።

መርሃግብሩ ቀጣይነት ያለው እንደሆነም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም