የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ለሠራዊት አባላት ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ለሠራዊት አባላት ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
117
አዲስ አበባ ታህሳስ 2/2013 (ኢዜአ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በትግራይ ክልል ህግ በማስከበር ላይ ላለው የመከላከያ ሠራዊት አባላት ልጆት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ማህበሩ ለሠራዊቱ ልጆች ያደረገው ድጋፍ 50 ሺህ ደብተር፣ 5 ሺህ እስክርቢቶ እና 5 ሺህ እርሳስ ነው።
ድጋፉን የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ፕሬዚዳንት አብነት ገብረመስቀል በምድር ኃይል ተገኝተው አስረክበዋል።
ማህበሩ ድጋፉን ያደረገው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ልጆች ጭምር ያለውን አጋርነት ለማሳየት መሆኑ ተገልጿል።
ለወደፊትም የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ድጋፉን የተረከቡት በመከላከያ ሚኒስቴር የፋይናንስ ሥራ አመራር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሊዊጂ ናቸው።
ሚኒስቴር ዴኤታዋ የስፖርት ማህበሩ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ድጋፉ ለመከላከያ ሠራዊት የሞራል ስንቅ እንደሚሆንም ነው የገለጹት።
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በቅርቡ በማይካድራ ከተማ በጁንታው ታጣቂ ሃይል ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰብ ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደርጋለሁ ብሏል።